Digital One ID Card System
Digital One ID Card System
ይህ ሲስተም ማለት አንድ የመታዎቂያ ካርድን በርከት ላሉ አገልግኖቶች መጠቀሚያ ሲሆን ዋና አላማውም የወረቀት አሰራርን መቀነስ ነው። ይህ ሲስተም ባርኮድን በመጠቀም የሚሰራ ሲሆን እንደ መታዎቂያ ካርድ እና እንደ መመገቢያ ካርድ መጠቀም ያስችላል። ይህም ማለት ተማሪዎች ወይም ሰራተኞች ይህን በባርኮድ የሚሰራ መታዎቂያ scan በሚያደርጉበት ጊዜ ማንነታችውን የሚገልጽ መርጃ (ሙሉ ስም፤ መታዎቂያ ቁጥር፤ የተምህርት ክፍል እና የፎቶ ምስል) ስክሪን/screen ላይ ያሳያል፤ የማይታወቅ መታዎቂያ scan ከተደረገ የ alarm ድምጽ ያሰማል። እንደመመገቢያ ስንጠቀምም ከሚያሳየው መረጃ በተጨማሪ ድጋሜ የሚገባ ካለ የ alarm ድምጽ ያሰማል። ይህም የዲጂታል መታዎቂያ ሲስተም አብሮ ይተካተተለት በ 1 ደቂቃ ከ 1000 በላይ መታዎቂያ ካርድ መስራት የሚያስችል ሶፍትዎር/software አለው። ከዚህም በተጨማሪ ይህ ሲስተም እንደ ማስታዎቂያ ቦርድ መጠቀም ያስችላል፤ ይህም ማለት መታዎቂያ scan ከተደረገ በኋላ እና ለ1ደቂቃ ያህል ጠብቆ scan የሚያደርግ ከለለ ወደ ማስታውቂያው ይቀየራል። ይህም ሲስተም በ network አማካኝነት ስለሚሰራ ከየትኛውም ቦታ ሆነን መመዝገብ፤ ማጥፋት፤ ማስተካከል እና የመሳሰሉትን ማድረግ ይቻላል። ይህ ሲስተም በ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ባህርዳር ኢንስቲትዩት ቴክኖሎጂ ተገጥሞ ካለፉት 9 ወራት ጀምሮ በምስራት ላይ ይገኛል።
Features:
1. በቀላሉ የሰዎችን ማንነት ለማዎቅ ያስችላል።
2.በየአመቱ ለመመገቢያ ካርድ የሚወጣን ወጪ ይቀንሳል።
3.ምን ያህል ተማሪ እንደተመገበ የሚያሳይ ረፖርት ይሰራልናል ይህም የሚያስፈልገንን የምግብ ፍጆታ ለማዎቅ ያስችለን ዘንድ ላቅ ያለ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
4.እንደ ማስታዎቂያ ቦርድ በመጠቀም የተለያዩ ማስታዎቂያዎችን በመለጠፍ ቶሎ ቶሎ እንዲታዩ ለማድረግ ያስችላል።
5.የደህንነት ችግረን ይቀንሳል ይህም ማለት fake መታዎቂያ ሰርቶም ሆነ አሰርቶ ለመግባት አያስችልም ።
6.ፈጣን በሚባል ጊዜ ማለትም በ 1 ደቂቃ ውስጥ ከ 1000 በላይ መታዎቂያዎችን ይሰራል።
2D Barcode Scanner
Raspberry pi
Lan port internet over USB
Vehicle Driver Sleeping Alert
Barcode based Attendance management system
ID making software (1000 IDs per 1 min)
Automatic Gate Barrier
Non contact infrared temperature sensor